ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት

አሰላ ቅርንጫፍ

             መግቢያ(Introduction)

      በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው።

ምስጋና ለአለማት ጌታና ተንከባካቢ ለሆነው አሏህ የተገባ ይሁን።

 የአሏህ ውዳሴና ሠላም ተወዳጅ፣አዛኝና ለጋሽ በሆኑት ነብያችን ሙሐመድ { } ላይ፣በባልደረቦቻቸውና የእርሳቸውን መንገድ በመልካም በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

እነሆ ኢስላማዊ መርሆ ላይ የተመሰረተ የአኗኗር ባህልና እሴት መገንባት በሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የተጣለ ግደታ ነው።በመሰረቱ እኛ የሰው ልጆች በዚች ምድር ላይ ምትኮች ሆነን ስንኖር በርከት ያሉ እና የተለያየ ገፅታ ያላቸው  የህይወት ገጠመኞችን እናስተናግዳለን።በተጨማሪም ይህ ጉዳይ ሁሉንም የሰው ዘር ሊያጋጥም የሚችልና ማንነትን፣ዘርን፣ቀለምን እንዲሁም እድሜን የማይለይ ሆኖ እናገኘዋለን።

ስለሆነም ማናችንም በሚደርስብን የህይወት ውጣ ውረድ የሸሪዓ መርሆን በተከተለ መልኩ እርስበርስ መደጋገፍና መረዳዳት ይኖርብናን። አንድ ሙስሊም በሚኖርበት አካባቢ ውስጥ በሚኖረው የህይወት መስተጋብሮችና ትስስሮች የሚስተዋሉ ደስታዎች፣ፈተናዎች፣ሃዘኖች፣መከራዎችና ከራሱ ጋር የተቆራኙ የህይወት ገጠመኞችን የሚያልፍበትን ግልፅና እንከን አልባ የሆነ መንገድን ዲናችን እስልምና አስቀምጦ እናገኛለን። ጀመዐን መገንባት፣እርስበርስ መረዳዳትና ሸሪዓን መሰረት ባደረገ መልኩ ለችግሮቻችን በጋራ መፍትሄ ማስቀመጥ ያለብን ስለመሆኑ ዲናችን  እንዲህ ሲል በአንክሮ ያስተምራል።

۝ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَئَانُ قَوْمٍ أَنْ صَدُّوكُمْ عَنِ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ أَنْ تَعْتَدُوا وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَاتَّقْوَى وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ وَاتَّقُوا الله إِنَّ الله شَدِيدُ الْعِقَابِ ۝ (سورة المائدة ۲)      

ከተከበረው መስጂደል ሃረም ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላትም (በእነርሱ ላይ) ወሰን እንድታልፉ አይገፋፋችሁ።በበጎ ነገርና አሏህን በመፍራትም ተረዳዱ ።ነገር ግን በሓጢዓትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ ።አሏህንም ፍሩ።አሏህ ቅጣቱ ብርቱ ነውና ።(ሱረቱ አል-ማዒዳ)

 ይህ የቁርዓን አንቀፅ የሚያስረዳን በሃጢዓትና ወሰን በማለፍ መተባበር እንደሌለብንና በሌላ በኩል ደግሞ በመልካም ተግባርና አሏህን በመፍራት ላይ መረዳዳት እንዳለብን ነው።ታዲያ ከምንሰራቸው መልካም ተግባራት መካከክል በየተኛውም ሁኔታ የተቸገሩ ሰዎችን ከጎናቸው በመቆም ችግራቸውን ማቅለል አልያም በአሏህ ፍቃድ  ከችግራቸው ሙሉ በሙሉ ማላቀቅ መቻል አንዱ ነው። ይህን በምናደርግበት ጊዜ  ከአሏህ የምናገኘው አጅር ትልቅ ስለመሆኑ ነብያችን ሙሃመድ( ) በሃድሳቸው እንዲህ ያብራሩልናል።

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم :(من نفس عن مؤمن كربة من كرب الدنيا نفس الله عنه كربة من كرب يوم القيامة ومن يسر على معسر يسر الله عليه في الدنيا والآخرة والله في عون العبد ما كان العبد في عون أخيه...الحديث)(رواه مسلم)

አቡ ሑረይራ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደዲላቸው) ባስተላለፉልን ሀዲስ ነብያችን () እንዲህ ይሉናል፡ከዱኒያ ችግሮች የሆነችን አንዲት ችግር ከአንድ አማኝ ላይ ያስወገደ ሰው አሏህ ከእርሱ ላይ የአኼራ ችግሮች ከሆኑት አንዲትን ችግር ያስወግድለታል።ችግሩ የከበደበትን ሰው ችግር ያገራ አካል አሏህ ለእርሱ በዱንያም በአኼራም ያገራለታል።አሏህ ባሪያውን በመርዳት ላይ ነው ባሪያው ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ።(ሙስሊም ዘግበውታል)

በዚህ መሰረት በችግር የሚሰቃዩ ወገኖች እንዳይኖሩና ሰዎች በሃዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ከኢስላማዊ የሸሪዓ መርሆ  ያፈነገጡና አሏህን የሚስቆጡ እንዳይሆኑ እርስበርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት ለየትኛውም ዘመን የሚስማማውን ትክክለኛውን የኢስልምና አስተምህሮት በተግባር ለመኖር የሁላችንም ያላሰለሰ ጥረት መኖር ይገባዋል። 

እነሆ ይህን ታላቅ እና የተቀደሰ ራዕይ በማንገብ በአሰላ እና አካባቢዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች በሙሉ ሚዛናዊ የሆነውን የእስልምና ስልታዊ አኗኗር ተደራሽ ለማድረግ እና ከአሏህ በመቀጠል ሰበብ የሆነውን የሰውን ልጅ ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን ለመርዳት ያስችለን ዘንድ “ በጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አሰላ ቅርንጫፍ “ የተሰኘ ተቋም መመስረታችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው::

1. ተቋሙን የመመስረት አስፈላጊነት/Rationale/

  ሃዘን እና ደስታን ጨምሮ ሰዎች በሚኖራቸው የትኛውም ማህበራዊ መስተጋብር የዲን ግንዛቤን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው ይፈለጋል::ከዚህም ባሻገር የተቸገሩ ሰዎችን በተቀናጀ መልኩ ማገዝ እና መርዳት ያስፈልጋል:: ስለሆነም  እንደ አሰላ ከተማ በዚህ ረገድ ተቀናጅቶ የሚንቀሳቀስ ተቋም ባለመኖሩ ይህን ጉዳይ የትኩረት ማዕከል በማድረግ ለመስራት የሚያስችል ተቋምን መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት የተሰኘ ተቋምን መስርተናል::

2. ራዕይ/vision/

በጎ አድራጎት ድርጅቱ በቀጣይ በሚሰራቸው ስራዎች ውጤታማ ሆኖ ይረዳቸው  የነበሩ ወገኖች ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ረጂ ሆነው ማየት ነው

3. ተልዕኮ/mission/

ከአሏህ በመቀጠል የሰውን ልጅ እገዛ የሚሹ ወገኖቻችንን በመርዳትና ከጎናቸው በመቆም ከችግር የተላቀቀ ማህበረሰብ በማፍራት የሀገራችንን እድገት ለማፋጠን መትጋት

4. የድርጅቱ ዓላማዎችና የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

1. በህይወታችን ውስጥ በሚያጋጥሙን ሃዘን እና ደስታ ላይ እርስበርስ በመረዳዳት እና በመተጋገዝ ኢስላማዊ ህገ-ደንቦችን ተፈፃሚ ማድረግ

2. ችግርን መቋቋም ለሚሳናቸው፤ እንዲሁም ሃዘን እና ደስታን በራሳቸው መወጣት ለሚያዳግታቸው አቅመ ደካማ ወገኖቻችን ዲናችን በሚያዘን መልኩ ከጎናቸው በመቆም ልዩ ድጋፍ ማድረግ

3. ጧሪ ያጡ አረጋዊያንንና አካል ጉዳተኛ የሆኑ ወገኖቻችንን መርዳት እና መንከባከብ

4. ወላጅ አልባ(የቲም) ለሆኑ ህፃናት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እና ማቋቋም

5. በቂ ገቢ ለሌላቸውና ረዳት(ባል) አልባ ለሆኑ ሴቶች ድጋፍ በማድረግ ከተረጅነት ማላቀቅ

6. በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ወገኖቻችን አስፈላጊውን የዓይነት ድጋፍ ማድረግ

7. በረመዳን ፆም ወቅት የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ወገኖቻችንን የወር አስቤዛ መሸፈን 

8. ከረመዳን ፆም በሗላ ለዘካተል ፊጥር ተገቢ የሆኑ ሰዎችን በመለየት ዘካውን በተገቢው መንገድ ማዳረስ

9. ከተለያዩ አካላት ወጪ የሚደረጉ የዘካተል ማል ሶደቃዎችን በመቀበል ለዘካው ተገቢ ለሆኑ ሰዎች ተደራሽ ማድረግ

10. በኡዱህያ ጊዜ መሳኪኖችን በመለየት እንደማንኛውም ሙስሊም በዒዱ ቀን ደስተኛ ሆነው እንዲውሉ ከኡዱህያ ስጋ ጀምሮ አስፈላጊውን ዲጋፍ ማድረግ

11. የተሟላ የጀናዛ ማጠቢያ በማቅረብ የጀናዛ እጥበት አገልግሎት መስጠት

12. የድንኳን አገልግሎት መስጠት

13. የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ሰዎች የከፈን፣የቀብር ቁፋሮና መሰል ወጭ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮችን መሸፈን 

14. የአስክሪን መሸኛን በማቅረብ የጀናዛ ሽኝት አገልግሎት መስጠት

15. የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው ሰዎች የተለያዩ የዓይነት(ምግብና አልባሳት) ድጋፎችን ማድረግ

16. በአጠቃላይ በችግር የሚሰቃዩ ወገኖቻችን በአላህ ፍቃድ ካሉበት ችግር ተላቀውና እንደማንኛውም ሰው ራሳቸውን ችለውና አንገታቸውን ቀና አድርገው ለማየት እንድንበቃ መስራት

17.  የተለያዩ የቂርዓትና የዳዕዋ አውዶዎችን፣ፒድዔፎችን እንዲሁም ፓፕሌቶችን በአማርኛና ኦሮሞኛ ቋንቋዎች መጫንና ማሰራጨት

18. የተለያየ ይዘት ያላቸው የአረበኛ ኪታቦችን፣ወደ አማርኛና ኦሮሞኛ ቋንቋ የተተረጎሙ መፅሀፍቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ        

5. በበጎ ስራው ለመሳተፍና አባል ለመሆን  

ü  የአባልነት ፎርሙን መሙላት

ü   የተቸገሩ ሰዎችን የመርዳት ንያን(ሀሳብን) ማንገብ

ü  የዚህ ስራ አጅር(ምንዳ) ከአሏህ ብቻ እንደሆነ ማመን

 

አድራሻ- ቀበሌ 07 አል-ኑር መስጂድ ፊት ለፊት በሚገኘው

 በርሄ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል!!

ስልክ 0925973317/0911491371

የባንክ ቁጥር ፦ ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አሰላ ቅርንጫፍ

ዘምዘም ባንክ/0018575710301                ሂጅራ ባንክ/20039 

ኢት/ያ ንግድ ባንክ/1000518322978          አቢሲኒያ ባንክ/122351858

         

                  ق قال النبي : " التقوا النار ولو بشق تمرة " (متفق عليه)

                    የአሏህ መለዕከተኛ(): “የቴምር ክፋይ መፅውታችሁም 

               ቢሆን  ከእሳት ተጠበቁ  (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

۩ ይህን መልዕክት አባዝታችሁ መበተን ለምትፈልጉ ወንድምና እህቶች ፍቃደኞች

መሆናችንን ከወዲሁ እየገለፅን አሏህ መልካም ጀዛዕን እንዲከፍላችሁ እንመኛለን።

 

 

 

 






 

        

 

 

 

 

 

 

 

Comments

Popular posts from this blog

የጉራጌዉ ዞን ሴራ!!!

ዋቻሞ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ይቁም።

የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊምች ጉዳይ እውነታው ምንድነው? ከይት ወደ የት? ከብዙ ጥቂቱ--