የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊምች ጉዳይ እውነታው ምንድነው? ከይት ወደ የት? ከብዙ ጥቂቱ--



ጉንችሬ የተሰገሰገው ጎንደር ያለው የሰሜኑየኦርቶ ፅንፈኛ ቡድን በተለያዩ ጊዜያቶች ሙስሊሙ ለመጉዳት ጥረት እያደረገ ቆይቶዋል ። አካባቢው ላይ የፈጠሩወቸው ትንኮሳዎች ብዙ ቢሆኑም በጥቂቱ ለመግለፅ ያህል ትምህርት ቤቶች ላይ ሙስሊም ሴቶች ሻሽ እንኩዋን ለማሰር  እንዲሁም ሒጃብና ጅልባብ ተከልክለው በተለያዩ ጊዜያት ከትምህርት ተገለው ሙስሊሙ እስከ ፌደራል ድረስ ተከከራክሮ መብቱን አስከብሮዋል። ተማሪዎች ሲሰግዱ በመደብደብ በማንቋሸሽ የፈፀሙት ግፍ የማይረሳ ነው ። 2003 ላይ ሁለት ሴት ተማሪዎች ጅልባብ ለምን ለበሱ ብለው ከቸርች ነጠላ ለብሰው ት/ቤት ካልገባን ሞተን እንገኛለን በማለት ትምህርት አስተጓግለው ከሙስሊሙ ጥረትና ትግል ቦሀላ እንደ አገር በጅልባብ አፋቸው እንዳይከፍቱ አድርጎዋል ።


ከላይ በተዘረጋው የመሀበረ ቅዱሳን ሰንሰለታቸው መሰረት ሙስሊሙ መሀበረሰብ ላይ የቀብር ቦታ በመከልከል የቀብር ቦታ ላይ ካርታ በማውጣት በሊዝ መሸጥ በመሞከር በአግባቡ ሙስሊሙን ያማከለ የመስጂድ ቦታ ባለ መስጠት  ያሉን የመስጂድ ቦታዎች ካርታ በመከልከል ጫና ፈጥሮዋሉ። ከተማው ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ ግብር ያለአግባብ በመጫን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን ስልጣን እንዳያገኙና ስልጣን በኦርቶ ቢቻ እንዲያዝ በማድረግ በሰንሰለት ሙስሊሙን ጎድተዋል። ለአብነት ያክል የጉንችሬ ሙስሊም መቃብር በዚሁ ፅንፈኛ ሰንሰልት በወቅቱ የወረዳው አስተዳደር የነበረው በያቆብ ግርማ አዛዥነት በሊዝ እንዲሸጥ በመሸንሸን፣ ቀብሩ ላይ መንገድ የማውጣት ሴራ በሙስሊም ረብረብ ከሽፎዋል ። በጉንችሬ ከተማ በኢንቨስተር ኢንጂነር ቸሩ መዋእለ ህፃናት ተከፍቶበት የሚጠቀምበት ቦታ በያቆብና በኢንቨስተሩ  አዛዥነት ወደ ቸርች ለመቀየር ቢጥሩም ቦታው የት/ቤተ ነው ብሎ ሙስሊሙ መሀበረሰብ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ አረጎዋል ። እንዲሁም ብዙ የወል መሬቶች ወደ ቸርችነት ተቀይሮዋል ለምሳሌ በኮሰድ ቀበሌ ጋረራ ቸርች መጥቀስ ይቻላል። ሰንሰለታቸው ምን እንደሆነ ዘመድኩን በቀለ በጩኸቱ አሳይቶናል።


አሁን ጉንችሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እየሆነ ያለው ነገር እውነታው ምንድነው?????


አምና 2014 ግንቦት ላይ የኦርቶዶክስ ተማሪዎች ተርሆኘ ት/ቤት ከአራት አመት በላይ ኒቃብ ከለበሱ ሴቶች ጋራ አንማርም በማለት አንማርም ብለው ትምህርት እንዲቋረጥ ተደርጎ በመሀበረሰቡ ጥረት አሁንም ትንኮሳ ባይቆምም ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል። አስቡት እዛው ት/ቤት ተምርዉ ተመረቀው መሀበረሰቡ በማገልገል ላይ እህቶች እያሉ ለምን ትንኮሳው ተፈለገ ?። ተረሆኘ ት/ቤት የከሸፈበት ቡድን የያቆብ ግርማ ስልጣን በመጠቀም ረበሻው ወደ ወረዳው ከተማ ጉንችሬ ት/ቤት በማምጣት ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ከሙስሊም ጎን እንዳይቀመጡ ተለይተው በመቀመጥ ጀምረው ፈተና ሊደርስ አካባቢ የአምስት አመት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ሴቶች ካላወለቁ ፈተና አንፈተንም በማለት ት/ቤት በጥብጠዋል። ከቸርች እየዘመሩ በቄስ ተመርተዎ ነጠላ ለብሰው በመግባት የፀሎት ሰአት ይፈቀድልኝ በማለት ት/ቤት አዘግተዋል። ት/ቤቱ ፋይናል መፈተን ባለመቻሉ ተማሪዎች ሳይማሩና ሳይፈተኑ ወደ ቀጣይ ክፍል አልፈዋል። ት/ቤት ግቢ ከቸርች ቄስ ይዘው ገብተው ጠዋፍ አብርተው ሙስሊም ሴቶች በኒቃብ አይማሩም ብለው ሲበጠብጡ ማንም ምንም አላላቸውም ነበር። ከጉንችሬ ት/ቤት አልፎ ወደ ሌሎች ሁለት ት/ቤቶች ማለትም ጋርባዶና እገዜ ሁለተኛ ደረጃ  ት/ቤት በተመሳሳይ ሁኔታ ረብሸዋል ግን ምንም አልተባሉም። እገዜ ት/ቤት ላይ በዚህ ጉዳይ ትንቀሳቀሳላችሁ በማለት 47 ሙስሊም ተማሪዎች ተባረዋል ። የ 16 አመትዋ ኢክራም ኒቃብ ለበስሽ ተብላ ከታሰረች አንድ ወር አልፎዋታል ። በዚህ ጉዳይ ሲሳተፋ የተገኙ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ሲያከማቹ ትምህርት ቤት ሳያቃጥሉ ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች ግን ለፍርድ ሳይቀርቡ ኦርቶዶክስ በመሆናቸው ተትተዋል። ሙስሊሙ ግን ያለ ጥፍቱ በእስር እያንገላቱት ነው።


ጉንችሬ ላይ ከብዙ የሽማግሌ ጥረት ቦሀላ ት/ቤት እንዲጀመር ቢደረግም የኦርቶዶክስ ተማሪዎች ግን ከታች በምትመለከቱት መልኩ በመበጥበጥ ትምህርት አስቁመው። አለፍ ሲልም የት/ቤት ኘላዝማ ዘርቀዋል የተማሪ ዶክመንት አቃጥለዋል ሙስሊሞችን ደብድበዋል ለህግ እንኩዋን አልቀረቡም።ከክልል እስከ ወረዳ ባለ የኦርቶዶክስ ባለስልጣን በመጠቀም ሙስሊሙ ገሸሽየ የሚያደርግ መመሪያ ያለ አግባብ በማውጣት ሙስሊሙ ከትምህርት አፈናቅለው 1500 ተማሪ ትምህርት ላይ አይደለም። የትምህርት ቤቱ አርአያ የሆኑ እንዲሁም በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ መከረም ትግስቱን ጨምሮ ሶስት የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች አባረዋል ኢስሀቅ በድሩና አብዱል መሊክን አስረዋተዋል። ይባስ ብሎ ለእህቶች መብት የተከራከሩ ወጣቶችና ሽማግሌዎች እንዲሁም ተማሪዎች እስር ላይ ናቸው። የታሰሩ ወንድሞች 14 ሲሆኑ አራት ተማሪዎች ይገኙበታል ከትምህርት የተባረሩም ሶስት ተማሪዎችም አሉ። እንዲሁም ሙስሊም መምህራን ተለይተው ታስረዋል ከቦታቸው በግፍ እንዲነሱ ተደረጎዋል ። አካባቢው ያሉ ሙስሊም ወጣቶች በልዩ ሀይል በማስፈራራት ተባረዋል ተሰው ነው ያሉት። ከዚህ በፊት ከሀያ በላይ ወጣቶች እስር ቤት ታጉረው ተፈተዋል። 


በጉንችሬ እስር እና ማሳደዱ ቀጥሏል:: አሁን ላይ በእስር የሚገኙ ሙስሊሞች ስም ዝርዝር መረጃው ደርሶናል::


ከታሳሪዎቹ መካከል 

1. ተማሪ ኢክራም -ታዳጊ የ16 አመት ሴት ተማሪ 

ኧገዜ ከሚባል አካባቢ የታሰሩት:-


የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ስም ዝርዝር

1, አክመል ሀዲ

2, ከድር ሶሜጋ

3, ሀምዛ አህመድ

4, ታደለ አማን

5,ዝያድ ነክር

6, ፈይዱ ሻሚል

7, ከይራት ጉዱ

8, ጅላሉ 

9, ሰይድ

10, ረመዳን (ከእስር በ10ሺህ ብር በዋስ የተፈታ ሲሆን በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ራሱን ስቶ የነበረና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት)


ከጉንችሬ በእስር ላይ የሚገኙ

1, አባታችን ዲንሰፋ ኑሩ

2, አብዱልማሊክ ሸዋበዛ የ12ኛ ክፍል ተማሪ

3, ኢስሃቅ በድሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ናቸው

4,ሙከረም ትግስት የ12ኛ ክፍል ተማሪ

Comments

Popular posts from this blog

የጉራጌዉ ዞን ሴራ!!!

ዋቻሞ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ይቁም።