ዋቻሞ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ይቁም።

 

በደቡብ ክልል ከምባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በአንድ መስጂድ ውስጥ ጥሰው በመግባት ፈጸሙት በተባለ ጥቃት አምስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡


የድብደባ ጥቃቱ የደረሰው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ አቅራቢያ በሚገኝና አላስካ በተባለ መስጂድ ውስጥ ነው፡፡

ድብደባ የደረሰባቸው ወጣቶች በሙሉ የዱራሜ ካምፓስ ተማሪዎች መሆናቸውን ምንጮች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡

በስፍራው ነበርኩ ያሉ አንድ የአይን እማኝ ለጥቃቱ መነሻ የሆነው አንድ ወጣት በመስጂድ ውስጥ በመግባት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ መያዙን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተያዘውን ወጣት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ለማድረስ ሲሞከር ሁኔታውን የተቃወሙ ሌሎች ወጣቶች በቡድን በመሰባሰብ ወደ መስጂዱ ቅጥር ግቢ በመግባት የዱላ ጥቃት  ማድረሳቸውንም እኝሁ የአይን እማኝ ገልጸዋል፡፡

አካላዊ ጥቃት የደረሰባቸው አምስት ተማሪዎች ወደ ዱራሜ ሆስፒታል መምጣታቸውን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጡት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ማቴዎስ በበኩላቸው አሁን ላይ ለተጎጂዎቹ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል፡፡

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት ለገሠ በበኩላቸው ሁኔታው ሊከሰት የቻለው ከስርቆት ጋር በተያያዘ በተነሳ አለመግባባት ነው ብለዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችን ወደ ህክምና፤ የተቀሩትን ደግሞ እንዲረጋጉ በማድረግ የትምህርት ሂደቱ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ለማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ከተማሪዎችና ከከተማው የፀጥታ አካላት አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን የጠቀሱት ዶ/ር ዳዊት ጉዳት የፈጸሙ ግለሰቦች በህግ የሚጠየቁበት ሂደት መጀመሩን አስረድተዋል፡፡

#ዶቼ_ቬለ

Comments

Popular posts from this blog

የጉራጌዉ ዞን ሴራ!!!

የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊምች ጉዳይ እውነታው ምንድነው? ከይት ወደ የት? ከብዙ ጥቂቱ--