Posts

Showing posts from February, 2023

ዋቻሞ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ይቁም።

Image
  በደቡብ ክልል ከምባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በአንድ መስጂድ ውስጥ ጥሰው በመግባት ፈጸሙት በተባለ ጥቃት አምስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ የድብደባ ጥቃቱ የደረሰው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ አቅራቢያ በሚገኝና አላስካ በተባለ መስጂድ ውስጥ ነው፡፡ ድብደባ የደረሰባቸው ወጣቶች በሙሉ የዱራሜ ካምፓስ ተማሪዎች መሆናቸውን ምንጮች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡ በስፍራው ነበርኩ ያሉ አንድ የአይን እማኝ ለጥቃቱ መነሻ የሆነው አንድ ወጣት በመስጂድ ውስጥ በመግባት ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ መያዙን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተያዘውን ወጣት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ለማድረስ ሲሞከር ሁኔታውን የተቃወሙ ሌሎች ወጣቶች በቡድን በመሰባሰብ ወደ መስጂዱ ቅጥር ግቢ በመግባት የዱላ ጥቃት  ማድረሳቸውንም እኝሁ የአይን እማኝ ገልጸዋል፡፡ አካላዊ ጥቃት የደረሰባቸው አምስት ተማሪዎች ወደ ዱራሜ ሆስፒታል መምጣታቸውን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጡት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ማቴዎስ በበኩላቸው አሁን ላይ ለተጎጂዎቹ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል፡፡ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የዱራሜ ካምፓስ ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት ለገሠ በበኩላቸው ሁኔታው ሊከሰት የቻለው ከስርቆት ጋር በተያያዘ በተነሳ አለመግባባት ነው ብለዋል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችን ወደ ህክምና፤ የተቀሩትን ደግሞ እንዲረጋጉ በማድረግ የትምህርት ሂደቱ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ለማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ከተማሪዎችና ከከተማው የፀጥታ አካላት አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉን የጠቀሱት ዶ/ር ዳዊት ጉዳት የፈጸሙ ግለሰቦች በህግ የሚጠየቁበት ሂደት መጀመሩን አስረድተዋል፡፡ #ዶቼ_ቬለ

የጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሙስሊምች ጉዳይ እውነታው ምንድነው? ከይት ወደ የት? ከብዙ ጥቂቱ--

ጉንችሬ የተሰገሰገው ጎንደር ያለው የሰሜኑየኦርቶ ፅንፈኛ ቡድን በተለያዩ ጊዜያቶች ሙስሊሙ ለመጉዳት ጥረት እያደረገ ቆይቶዋል ። አካባቢው ላይ የፈጠሩወቸው ትንኮሳዎች ብዙ ቢሆኑም በጥቂቱ ለመግለፅ ያህል ትምህርት ቤቶች ላይ ሙስሊም ሴቶች ሻሽ እንኩዋን ለማሰር  እንዲሁም ሒጃብና ጅልባብ ተከልክለው በተለያዩ ጊዜያት ከትምህርት ተገለው ሙስሊሙ እስከ ፌደራል ድረስ ተከከራክሮ መብቱን አስከብሮዋል። ተማሪዎች ሲሰግዱ በመደብደብ በማንቋሸሽ የፈፀሙት ግፍ የማይረሳ ነው ። 2003 ላይ ሁለት ሴት ተማሪዎች ጅልባብ ለምን ለበሱ ብለው ከቸርች ነጠላ ለብሰው ት/ቤት ካልገባን ሞተን እንገኛለን በማለት ትምህርት አስተጓግለው ከሙስሊሙ ጥረትና ትግል ቦሀላ እንደ አገር በጅልባብ አፋቸው እንዳይከፍቱ አድርጎዋል ። ከላይ በተዘረጋው የመሀበረ ቅዱሳን ሰንሰለታቸው መሰረት ሙስሊሙ መሀበረሰብ ላይ የቀብር ቦታ በመከልከል የቀብር ቦታ ላይ ካርታ በማውጣት በሊዝ መሸጥ በመሞከር በአግባቡ ሙስሊሙን ያማከለ የመስጂድ ቦታ ባለ መስጠት  ያሉን የመስጂድ ቦታዎች ካርታ በመከልከል ጫና ፈጥሮዋሉ። ከተማው ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ ግብር ያለአግባብ በመጫን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችን ስልጣን እንዳያገኙና ስልጣን በኦርቶ ቢቻ እንዲያዝ በማድረግ በሰንሰለት ሙስሊሙን ጎድተዋል። ለአብነት ያክል የጉንችሬ ሙስሊም መቃብር በዚሁ ፅንፈኛ ሰንሰልት በወቅቱ የወረዳው አስተዳደር የነበረው በያቆብ ግርማ አዛዥነት በሊዝ እንዲሸጥ በመሸንሸን፣ ቀብሩ ላይ መንገድ የማውጣት ሴራ በሙስሊም ረብረብ ከሽፎዋል ። በጉንችሬ ከተማ በኢንቨስተር ኢንጂነር ቸሩ መዋእለ ህፃናት ተከፍቶበት የሚጠቀምበት ቦታ በያቆብና በኢንቨስተሩ  አዛዥነት ወደ ቸርች ለመቀየር ቢጥሩም ቦታው የት/ቤተ ነው ብሎ ሙስሊሙ መሀበ...